በትግራይ የሥልጣን ሽግግር ዙሪያ የተፈጠረው ውዝግብ፦ የአውራምባ ታይምስ ዘገባ እና የአቶ አማኑኤል አሰፋ ጠንካራ ምላሽ
በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ውስጥ እየታየ ነው የተባለውን የሥልጣን ሽግግር እና የአመራሮች ምደባ አስመልክቶ በአውራምባ ታይምስ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ የቀረበው ዘገባ፣ በአሁኑ ወቅት የክልሉን ፖለቲካዊ መድረክ በእጅጉ አነጋጋሪ አድርጎታል። ለቀረበው ዘገባ ደግሞ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝዳንት እና የህወሃት ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ አማኑኤል አሰፋ የሰጡት ምላሽ ጉዳዩን ወደ ላቀ ደረጃ አሸጋግሮታል።
ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ በአውራምባ ታይምስ በኩል ባስተላለፈው መረጃ፣ አሁን ያሉትን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደን የሚተኩ አዲስ እጩ ፕሬዝዳንት መዘጋጀታቸውን ገልጿል። ጋዜጠኛው በዘገባው እንዲህ ብሏል፦
አሁን ያሉት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደን የሚተኩ አዲስ እጩ ፕሬዝዳንት ተዘጋጅቷል መባሉን ሰምተናል። እኚህ እጩ ፕሬዝዳንት ባለፈው ሳምንት ነበር ኃላፊነት እንዲረከቡ ታስቦ የነበረው፤ ሆኖም ጀነራል ታደሰ ፍቃደኛ ባለመሆናቸው እስከሚቀጥለው መጋቢት 30 ድረስ በትግስት እንዲጠብቁ ተነግሯቸዋል።
ዳዊት ከበደ አክሎም የእጩውን ማንነት እና በስተጀርባ ያለውን የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ሲያብራራ፦
ህወሃት ለዚህ ሀላፊነት የመደበቻቸው ሹመኛ በአሁኑ ጊዜ የጊዜ አስተዳደሩ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የህወሃት ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ አማኑኤል አሰፋ መሆናቸውን የገለጹልን ምንጮች፣ አቶ አማኑኤል ለእጩነታቸው በህወሃት ቀርቦ ዘጠኝ አባላት ባሉት የካውንስል ስራ አስፈጻሚ ውስጥ በስምንቱ ይሁንታ እንደተሰጣቸው አረጋግጠናል።
ከዚህም ባለፈ አቶ አማኑኤል አሰፋ ከፌደራል መንግስት ጋር ምስጢራዊ ግንኙነት ማድረጋቸውን እንዲህ ሲል ዘግቧል፦
አቶ አማኑኤል አሰፋ በተገባደደው ሳምንት አጋማሽ አዲስ አበባ ባሉ ባለሃብቶች አማካኝነት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የቅርብ ሰዎች ጋር ምስጢራዊ ውይይት ማድረጋቸውን ለባለሀብቶቹ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ለአውራምባ ታይምስ አረጋግጠዋል።
የአቶ አማኑኤል አሰፋ ጠንካራ ማስተባበያ እና ትችት
ለዚህ ዘገባ ምላሽ የሰጡት አቶ አማኑኤል አሰፋ፣ መረጃውን ሙሉ በሙሉ መሰረተ ቢስ እንደሆነ በመግለጽ የጋዜጠኛውን ሙያዊ ብቃት ጥያቄ ውስጥ ከትተዋል። አቶ አማኑኤል እንዲህ ሲሉ ምላሻቸውን ሰጥተዋል፦
ውድ ወንድም ዳዊት ከበደ፣ ስለ እኔ ያስተላለፍከው መረጃ ሙሉ በሙሉ የተሳሳተ ነው። እንደምታውቀው፣ ልምድ ያለው ጋዜጠኛ ስለማንኛውም ሰው መረጃ (ዜና) ለማቅረብ ባለቤቱን እውነቱን መጠየቅ ህጋዊ እና ሙያዊ ግዴታ መሆኑን ማሳሰብ አስፈላጊ ነው ብዬ አላስብም።
በተለይም ስለ ሹመቱ እና ስለ ምስጢራዊው ግንኙነት የቀረበውን ነጥብ እንዲህ ሲሉ አጣጥለውታል፦
ያም ሆነ ይህ፣ የተለቀቀው መረጃ ዓላማ ምንም ይሁን ምን፣ ስለ ኃላፊነት ምደባ ወይም ከሺቫ (ፌደራል) ጋር ስለተደረገው ውይይት ስለ እኔ ‘አገኘሁት’ ያሉት መረጃ አሁንም ነጭ ውሸት ነው።
አውራምባ ታይምስ በክልሉ አመራር ውስጥ ያለውን ክፍተት ሲያብራራ፣ ጀነራል ታደሰ ወረደ በአሁኑ ወቅት የተመሰረተውን የካውንስል አደረጃጀት “ህጋዊነት እና ተጠያቂነት” እንደሚጠራጠሩ ጠቅሷል። በዘገባው መሠረት፦
ጀነራል ታደሰ በካውንስል ስብሰባ ላይ ከተሳተፉ ረጅም ጊዜ እንደሆናቸው በማስታወስ፣ የአቶ አማኑኤል ሹመትን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ሰሞነኛ ውሳኔዎች የጸደቁት ጀነራል ታደሰ ባልተገኙበት መሆኑን አረጋግጠናል።
በተጨማሪም አዲሱ ፕሬዝዳንት (አቶ አማኑኤል) ቢሾሙ እንኳ ስልጣናቸው ውሱን እንደሚሆንና ወሳኝ ጉዳዮች በዶክተር ደብረጽዮን በሚመራው ካውንስል ስር እንደሚሆኑ ዘገባው አመልክቷል። በአውራምባ ታይምስ የቀረበው ዘገባ በትግራይ ከፍተኛ አመራሮች መካከል ያለውን አለመግባባት የሚያሳይ ቢሆንም፣ የአቶ አማኑኤል አሰፋ “ነጭ ውሸት” የሚል ማስተባበያ ደግሞ የመረጃውን ትክክለኛነት ከፍተኛ ጥርጣሬ ላይ ጥሎታል።
———————————————————————————————————————
የአውራምባ ታይምስ ዘገባ ቃል በቃል እንሆ፡
ዛሬም እንደ ሁልጊዜው በሶስት አንኳ እንኳን ነጥቦች ላይ ትኩረት አድርገን ነው መረጃዎቹን የምናቀርብላችሁ ተመልካቾች።
አሁን ያሉት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደን የሚጠቃ አዲስ እጩ ፕሬዝዳንት ተዘጋጅቷል መባሉን ሰምተናል። እኔ እጩ ፕሬዝዳንት ማናቸው? በምን አይነት ሂደት ተመረጡ በዝርዝር እንመለስበታለን። እኔ እጩ ፕሬዝዳንት ባለፈው ሳምንት ነበር ኃላፊነት እንዲረከቡ ታስቦ የነበረው ሆኖም ጀነራል ታደሰ ፍቃደኛ ባለመሆናቸው እስከሚቀጥለው መጋቢት 30 ድረስ ለሚቀጥለው 22 ቀናት መሆኑ ነው በትግስት እንዲጠብቁ ተነግሯቸው በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ። ተመልካቾች በዝርዝር የምናቀርበው ይሆናል።
በሁለተኛ ደረጃ የምንመለከተው ነጥብ አንድ የህወሃት ከፍተኛ አመራር ከአራት ኪሎ ሰዎች ጋር ምስጢራዊ ግንኙነት አድርገዋል መባሉ ነው። ይህ ግንኙነት እያወዛገበ እንደሆነ ተገልጿል። በአንድ በኩል የህወሃት ጓዶቻቸው ሳያውቁ አዲስ አበባ ባሉ ባለሃብቶች ባለሀብት የሆኑ ወዳጆቻቸው በኩል ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የቅርብ ሰው ጋር ተገናኝተዋል የተባለው ይህንንም በዝርዝር የምንመለስበት ይሆናል።
ከዚህ በተጨማሪ በሶስተኛ ደረጃ የምንመለከተው ሌተናል ጀነራል ብርሃነ ነጋሽ ወይም ወንድም በይታይ በመባል የሚታወቁ ወታደራዊ አዛዥ ለአንድ ያልተጠበቀ ሹመት ታስተዋል ተብሏል። እሱንም በዝርዝር እንመለከተዋለን ተመልካቾች።
እነዚህን በዝርዝር ወደ ምናቀርብ ዝግጅት በዝርዝር ከመሄዳችን በፊት ባለፈው ባቀረብነው ዝግጅት ምክንያት ከባድ ፈተና ነው ያሳለፍነው። ተመልካቾች እንግዲህ የለፉት አምስት ቀናት በዚህ በካውንስሉ ዙሪያ ባቀረው ትችት ምክንያት ነው ከባድ ውግዛትን ያስተናገድነው። እንደምታስታውሱት ይህ ካውንስል ተጠሪነት ህጋዊነቱና ተጠያቂነቱ በተመለከተ ጥያቄ አንስተን ነበር። ምንጮቻችን መነሻ በማድረግም ስለ አሰራሩ በስሩ ስላሉ ኮሚቴዎች በርካታ ነገሮች አቅርበን በኛ እምነት ይህ ተጠሪነቱ፣ ህጋዊነቱ እና ተጠያቂነቱ ግራ የሚያጋባው ካውንስል መንግስት አቀጥራት አልበኝነትን የሚያበረታታ በመሆኑ ነበር የተቸዉ። በዚህ የተነሳ ነበር ከባድ ዘመቻ ሲከፈትብን የሰነበተው።
እንግዲህ እንደምታስታውሱት የ25 ደቂቃ ፕሮግራም ነበር ባለፈው ሃሙስ የሰራነው ተመልካቾች። ይህ የ25 ደቂቃ አጭር ፕሮግራም ለካውንስሉ ወይም ለተቸዉ አካል ድጋፍ ያላቸው ወይም ደግሞ በካውንስል ውስጥ ላሉ ሰዎች ሎያል የሆኑ ሚዲያዎች ላለፉት አምስት ቀናት ያህል በጣም የተጠናከረ ዘለፋ ሲሰነዝሩብን ነው የሰነበቱት። ህወሃትም ትላንት ባወጣችሁ ኦፊሻል መግለጫዋ በመጨረሻው ፓራግራፍ ላይ ህዝብን በሚዲያ ስም ወይም ደግሞ በአክቲቪዝም ስም ህዝብን እያሸበሩ ያሉ አካላት አደብ ሊገዙ ይገባል አይነት ትንሽ ማስፈራሪያ አዘል ክስ አቅርባለች። ስም ባጠቅስም ያው ምን እንደሚመለከት ግልጽ ነው። ምክንያቱ ሰሞኑን የነበረው ርዕሰ ጉዳይ ስለሆነ።
ተመልካቾች በዋናነት ግን ቅደም ብዬ እንዳልኩት እኛ ከተቸዉ አመራሮች ጋር የተለየ ጥቅምት ትስስር ያላቸው ሚዲያዎች እኛን የሚሰሩበት የቃላት ቃላት ሁሉ አጥሯቸው ቃላት ሁሉ ለመምረጥ ተቸገረው ተመልክተናል። ይህ ማለት ግን አንዳንድ በሃላፊነት ስሜት የተቹ ሚዲያዎች የሉም ማለት አይደለም። አንዳንዶቹ ሚዲያዎች ምንም እንኳን ያቀረብነው ይዘት መነሻ አድርገው ትችት ቢያቀርቡም መልእክቱን ባስተናገደ ሚዲያ ወይም ጉዳዩን ወይም ዜናውን ባቀረበ ሚዲያ ወይም ባቀረበ ጋዜጠኛ ላይ ሳይሆን ትኩረት ያደረጉት ሃሳቡ ምንድነው ተገቢ ነው ወይ በሚል በራሳቸው አስተሳሰብ በራሳቸው አሰላለፍ ጀነራል ታደሰ እንዴት እንደዚህ ይላሉ በሚል ነው ሃሳቡ ላይ ነው ትኩረት ያደረጉት።
በተለይ አንድ ሚዲያ በጣም ሊያሰቃችሁ ይችላል ይሄን ስገረ ተመልካቾች። አንዱ ሚዲያ እኛን ለመተቸት ሆለስ ሳይቀር ጋብዞ ነበር ይዞ የቀረበው። ትንሽ ፈገግ ሊያሰኛችሁ ይችላል እዚህ ምትመለከቱት ግለሰብ በቅርቡ ነው ከ አስር ቤት የወጣው ያው ስራ የለውም ሆለስ ነው። ግን ስድብ ይችላል በሚል ነው ተጠርቶ የመጣው ስድብ ይችላል በሚል እዚህ ሚድያ ላይ ተጋብዞ ያው ከሆለስ የሚጠበቅ ስድብ ሰድቦናል። በነገራችን ላይ ይህ ግለሰብ በአስገዶ መድፈርት ወንጀሎ እስር ቤት ቆይቶ የወጣ ሰው ነው። ኦሪጌ ያላችሁ ሰዎች በተለይ እዛ አካባቢ ያላችሁ ተጋሩ ስለሰውየው ሁኔታ በዝርዝር ታውቃላችሁ ሚካኤል ካሳሁን ይባላል። እዚህ በዝርዝር እንደምትመለከቱት ያኔ በአሜሪካ ሚዲያዎች የወጣ ዜና ነው ሚካኤል ካሳሁን በአስገዶ መድፈር ወንጀል እስር ላይ ነው የነበረውን ያው ብዙዎቻችሁ ታውቃ ታላችሁ።
እንግዲህ ከዚህ እስር ቤት ቅጣቱን ጨርሶ ወጥቶ ስራ ማግኘት አልቻለም። ያው ስራ ስለሌለው አንድ የሚሰደብ ሰው አለ እዚህ ሚዲያ ላይ ቀርበህ ተሳደብ ብለው ተከራይቶት በዛ መንገድ ተከራይተውት ነው መጥቶ እዚህ ሚዲያ ላይ ቀርበው የተሳደበው። ያው እንግዲህ ትንሽ ሊያስገርም ይችላል እንዲህ አይነት ነገር ያው ኖርማሊ እሱ ብቻ ሳይሆን እዚህ የምትመለከቱት ሆስቱም ከሱ የተለየ ታሪክ የለውም። ያው ብዙ ስለሰዎች ዝርዝር ጉዳይ ማውራት አንፈልግም። ግን ያው ወልዶ በመካድ የሚከሰስ በዚህ መልኩ ሲካሰስ የሚውል ግለሰብ ነው። ሁለቱም በመጥፎ ስነምግባር የሚታወቁ ለራሳቸው ክብር የሌላቸው በጣም የተጨማለቀ ስብዕና ያላቸው ናቸው።
ተመልካቾች በጣም ቅርን የምገልጸው የግድ መግለጽ ስላለብኝ። እንግዲህ ህውሃትን የሚያክል ሃገር ሲመራ የነበረ ድርጅት ስንት ሃሳብ የነበረው የራቸው ሰዎች የመሩት ድርጅት በዚህ ደረጃ ለምን ተተቸን በሚል ሆምለሶች የተከራዩ ሰውን የሚሰደቡ አመራሮች ማፍራት ችሏል። ይህ መሆኑ በጣም ነው የሚያሳዝነው። ዞሮ ዞሮ ዋናው አጀንዳችን እሱ ስላልሆነ እኛ ሃሳብ ማቅረብ ዜናዎች ሲኖር ማቅረብ መረጃ ምንጮቻችን መሰረት አድርገን ለህብረተሰቡ ይጠቅማል የምንላቸው መረጃዎች ነው ምናቀረበው። ምንም የተለየ ሚያሰዳድበን የሚያዘላልፈን ነገርም የለም። እንደዛም ሆኖ ግን ያው ያሳልፍናቸው አምስት ስድስት ቀናት በጣም ፈታኝ የነበሩ ከገለጽነው ሁኔታ አንጻር ተመልካቾች።
እንግዲህ ይሄንን እንደ መግቢያ ከገለጽኩ በሚቀጥለው መሸጋገሪያ ሙዚቃ ደግሞ ወደ ዋናው ጉዳይ በዝርዝር እገባለው ተመልካቾች። ተመልሰናል ተመልካቾች እንግዲህ ቅድም ብዬ እንደገለጽኩት በዛሬው እለት ህወሃት ጀነራል ታድሰ ወረደን ይተካል ያለችውን አዲስ ፕሬዝዳንት መደቧን መመደቧን አስታውቃለች። እንግዲህ ከ2 ቀናት በኋላ ስልጣናቸውን በይፋ የሚጨርሱት ወይም ስልጣናቸው በይፋ የሚያበቃው የትግራይ ጊዜ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ የስልጣን ጊዜያቸው ሲያበቃ የሚተካቸው ፕሬዝዳንት በህወሃት ተመድቦ እየተጠባበቀ እንደሚገኝ ለህዋት ህፈት እጅግ ቅርብ የሆኑ አንድ የአረማ ታይምስ ምንጭ አረጋግጠውልናል።
ህወሃት ለዚህ ሀላፊነት የመደበቻቸው ሹመኛ በአሁኑ ጊዜ የጊዜ አስተዳደሩ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የህወሃት ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ አማኑኤል አሰፋ መሆናቸውን የገለጹልን ምንጮች አቶ አማኑኤል ለእጩነታቸው በህወሃት ቀርቦ 9 አባላት ባሉት የካውንስል ስራ አስፈጻሚ ውስጥ በስምንቱ ይሁንታ እንደተሰጣቸው አረጋግጠናል። አዲሱ ፕሬዝዳንት እጅግ የተገደበ ስልጣን እንደሚኖራቸው የጠቆሙን እነዚህ ምንጮች በዶክተር ደብረተ በጽዮን ሰብሳቢነት የሚመራው እና የተለያዩ ኮሚቴዎችን በስሩ ያቀፈው የካውንስ ስራ አስፈጻሚ ብዙዎችን ሃላፊነቶች ጠቅልሎ እንደሚይዝ በማውሳት ፕሬዝዳንቱ ከህዝብ መሰረታዊ አገልግሎቶች ጋር የተገናኙ የእለት እለት ተግባራትን ከማከናወን የዘለለ ይህ ነው የሚባል የመወሰን ሚና እንደማይኖራቸው አብራርተውልናል።
በአንድ መንግስት ውስጥ እጅግ ወሳኝ የሚባሉ እንደ ጸጥታ ፖለቲካ እና ኢኮኖሚን የመሳሰሉ ክላስተሮችን ካውንስሉ ቀደም ብሎ በመደባቸው ኮሚቴዎች አማካኝነት እንደሚመሩ የገለጹ ለነዚህ ምንጮች የኮሚቴዎቹ አስተማሪዎችም የስራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን የሚያቀቡት ለካውንስል ሰብሳቢ ማለትም ለዶክተር ደብረጽዮን እንጂ ለሚመደቡት ፕሬዝዳንት አለመሆን አረጋግጠናል። አቶ አማኑኤልም በዚሁ ሃሳብ በዚሁ አገባብ ተስማምተው ሃላፊነቱን ለመረከብ መወሰናቸውን ያረጋገጡን የጀነራል ታደሰ የስልጣን ዘመን ከማብቃቱ ከአንድ ወር በፊት ጀነራሉ መልቀቂያ እንዲያስገቡና አቶ አማኑኤል ቀደም ብለው ይህንኑ ስልጣን እንዲረከቡ ታስቦ ነበር ያሉት አሉ እነዚህ አብረንታዊ ስሚጮች ሆኖም ጀነራል ታደሰ ይህ አይነቱ ክብረን ነካሄድ አቁሙ ብለው ዶክተር ደብረጺዮን በማስጠንቀቃቸው አቶ አማኑኤል እስከ መጋቢት 30 ማለትም ለሚቀጥሉት 22 ቀናት በትግስት መጠበቅ ግድ እንደሆነባቸው ምንጮቻችን ጨምሮ አስረድተዋል።
የፌደራል መንግስት በዚህ አዲስ ምደባይ የሚኖረው አቋም ምን እንደሆነ እስካሁን በይፋ ባይታወቅም አቶ አማኑኤል አሰፋ በተገባለደው ሳምንት አቀማሽ አዲስ አበባ ባሉ ባለሃብቶች አማካኝነት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የቅርብ ሰዎች ጋር ምስጢራዊ ውይይት ማድረጋቸው ለባለሀብቶቹ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ለወራን በታይምስ አረጋግጠዋል። አቶ አማኑኤል ይህንን ምስጢራዊ ግንኙነት ያደረጉት ከህወሃት ጓዶቻቸው ጋር ተመካክረው ይሁን አይሆን ግን የታወቀ ነገር የለም። ይህንኑ ጉዳይ እንዲያጣሩልን ከጠየቅናቸው የህወሃት ጽህፈት ቤት ምንጮች አንዱ ምናልባትም የነ ወይዘሮ ፈትለወር ግፊት ከዚህ ጀርባ ሊኖር እንደሚችል ግምታቸውን ገልጸውልናል። ዝርዝሩን በቀጣይ ምናራው ይሆናል። ምናልባት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የቅርብ ሰው ጋር የተገናኘ አናኙት የህወሃት ጽህፈት ቤት ሃላፊዎች አውቀው ወይም የነሱ ግፊት ኖሮበት ነው ወይስ በርግጥ አቶ አማኑኤል በራሳቸው ውሳኔ እና በራሳቸው አካሄድ ነው እዛ ውሳኔ ላይ የደረሱት የሚል ምናልባት ወደፊት የምናጠራው ይሆናል። ተመልካቾቻችን ግን አቶ አማኑኤል ከአንድ የፌደራል መንግስት ሃላፊ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ቅርብ ከሆኑ ሰው ጋር አዲስ አበባ ባሉ ባለሃብቶች አማካኝነት መገናኘታቸውን ግን አውራታዊ ሳይስን ቬሪፋይ ያደረገው ትክክለኛ መረጃ ነው።
ተመልካቾች ከዚህ በፊት ባቀረብነው ዘገባ በስፋት እንደገለጽነው ከህወሃት፣ ከሰራዊት እና ከጊዜያዊ አስተዳደር የተወጣጡ ዘጠኝ አባላት ያሉት የካውንስል ስራ አስፈጻሚ እንደተቋቋመ እና ፕሬዝዳንት ታደሰም የካውንስልን ተጠያቂነት፣ ጥሪነትና ህጋዊነት ጥያቄ ውስጥ በመክተት እውቅና እንደነበት መዘገባችን ይታወሳል። ለተናል ጀነራል ታደሰ ቅርብ የሆነ አንድ ምንጭ ለአብራ አምባታ እንዳረጋገጠው ጀነራሉ በካውንስል ስብሰባ ላይ ከተሳተፉ ረጅም ጊዜ እንደሆናችሁ በማስታወስ የአቶ አማኑኤል ሹመትን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ሰሞነኛ ውሳኔዎች የጸደቁት ጀነራል ታደሰ ባልተገኙበት በስንት የካውስሎ አባላት መሆኑን አረጋግጠውለልናል።
እንግዲህ ተመልካቾች በዚሁ ወደ ሶስተኛው ነጥብ እናልፋለን። ሶስተኛው ነጥብ ሌተናል ጀነራል ብርሃን ነጋሽ ወይም መዲህንን የሚመለከት ነው። ሌተናል ጀነራል ብርሃን ነጋሽ ወይም ደግሞ በተለምዶ መዲህን በመባል የሚታወቁ አንጋፋ ታጋይ የትግራይ ሰራዊት ዋና አዛዥ እንዲሆኑ ቀደም ብለን የገለጽነው ከአሁን ስል ስምምነት ላይ መድረሱን ሰምተናል። ከአጋፋይ ህውሃት ታጋዮች መካከል አንድ የሆኑት እና ከህይወት ከህወሃት የተሻለ የጠራ ፕሮግራም ያለው የፖለቲካ ድርጅት የለም በሚል አወዛጋዊ ንግግራቸው ምክንያት ከአንድ ወር በፊት ከበድ ያለ ትችት ያስተናገዱት ጀነራል ብርሃነ ሰራዊቱን በዋና አዛዥነት እንዲመሩ መታጨታቸውን የሰማነው። ይህ ምደባ ሃሳብ የቀረበው ከህወሃት እና የተወሰዱ የሰራዊት አዛዦችም የዚህ ሃሳብ ደጋፊ እንደሆኑ ለሰራዊት አዛዥ ቅርብ የሆኑ ምንጮች አረጋግጠውልናል።
ቀደም ሲል ብርጋዴር ጀነራል ሀይለስላሴ ግርማይ ወይም ወንድም ቤተይ ይሄንን ሃላፊነት እንዲይዙ ታስቦ የነበረ ቢሆንም የሁሉም ማለትም የበርካታ የአርሚ አሳዛዦች እና የሁለት የግንባር አዛዦች በዚህ ሃሳብ ባለመስማማታቸው በሰውዬው ምርጫ ባለመስማማታቸው ሃላፊነቱ ሳይሰጣቸው እንደቀረ ከሳቸው ይልቅ ለተላር ጀነራል ብርሃነጋሽ ወይም ለወድም ቤተይ ቢሰጥ የተሻለ እንደሆነ ሃሳብ መቅረቡን ጠቁመውናል ግን የመጨረሻ ውሳኔ ላይ አልተደረሰም።
እንግዲህ ተመልካቾች ዛሬ እነዚህን አጫጭር መረጃዎች ለማቀርብ ነው የመጣነው አብራችሁን ስለቆያችሁ በጣም እናመሰግናለን በቀጣይም ሌሎች መረጃዎች እናንተ እናቀርባለን ሰላም።